ልክ አካላችን/ሰውነታችን ችግር ሊገጥመው እንደሚችእ የአእሞሯችንም ጤና ችግር ሊገጥመው ይችላል፡፡ በሌላ አገላለጽ ልክ ሆዳችን፣ ሳንባችን፣ ልባችን፣ ኩላሊታችን፣ አንጎላችን፣ ቆዳችን… እንደሚታመመው ስሜታችን፣ ድርጊታችን፣ አስተሳሰባችን፣ አረዳዳችን፣ እና ማመዛዘናችን ይታመማል፡፡ ማንኛውም ሰው ልክ በስኳር፣ በልብ፣ ብክለት ነክ በሆኑ በሽታዎች (ወባ፣ ኤች አይ ቪ፣ ቲቢ፣ ጉንፋን፣ አተት…) በሳንባ፣ በኩላሊት… ሕመሞች ሊጠቃ እንደሚችለው ሁሉ በአእምሮ ሕመምም ሊጠቃ ይችላል፡፡
ይህ የትምርት ደረጃን፣ ዘርን፣ እድሜን፣ ጾታን፣ ሀበትን፣ የመኖሪያ ቦታን ወይም ሀገርን አይለይም፡፡ ይህ ህመም ማንኛውም ሰው ላይ ማለትም ‹‹ከተራው ሰው›› እስከ ሀገር መሪው ‹‹ከየኔቢጤው›› እስከ ባለጸጋው፤ ከህጻን እሰከ ሽማግሌው፣ ከሴቱ እስከ ወንዱ፣ ከተማረው እሰካልተማረው፣ ከታዋቂው እስከማይታወቀው፣ ከሰራ አጥ አስከ ባበሙያው ይከሰታል፡፡ ገበሬውም፣ ሀኪሙም፣ ወዛደሩም፣ ሳይንቲሰቱም፣ መምህሩም፣ አማኙም፣ ‹‹እምነት አልባውም››፤ ሰባኪውም፣ ምዕመኑም አእምሮው ሊታመም ይችላል፡፡
የሚከተሉትን ‹‹ዓለምን የቀየሩ›› የተባለላቸውን ሰዎች እንደምሳሌ ማንሳት እንችላለን
ከደራሲዎች
Charles Dickens (depression), Leo Tolstoy (depression)
የቢዝነስ መሪዎች
Howard Hughes (depression & OCD), J.P. Morgan (depression), Ted Turner (depression)
ተመራማሪዎች/ሳይንትስቶች
Charles Darwin (depression), Sigmund Freud (depression), Stephen Hawking (depression) Sir Isaac Newton (depression)
የፖለቲካ አመራሮች እና ምሁሮች
አብርሀም ሊንከን፥ Alexander the Great (depression), Napoleon Bonaparte (depression), Barbara Bush (depression) Winston Churchill (depression), Thomas Jefferson (depression),
Schizophrenia ያለባቸው ታዋዊ ሰዎች ጥቂቶቹ
John Nash (የሂሳብ ተመራማሪ፣ ፐሮፌሰር እና የኖቤል ሽልማት አሸናፊ)
Peter green: ጊታሪስት Darrell
Hammond፡ ተዋናይ
Skip spence፡ ጊታሪት፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ
በእርግጥ ከሰው ሰው፣ ከቦታ ቦታ፣ ከባህል ባህል፤ ከእድሜ እድሜ የአእምሮ ህመም የመከሰቻ ጊዜው፣ ስርጭቱ፣ ባህሪዉና ጥንካሬው ሊለያይ ይችላል፡፡ ለህመሙ ያለን ምላሽ፣ ተጋላጭነት፣ ተጎጅነት እና የምንወስደው ህክምናም ሊለያይ ይችላል፡፡
ታዲያ ጤና እክል ምንድን ነው?
ሁሉንም ባለሞያዎች ሊያስማማ የሚችል አንድ ቋሚ ፍቺ መስጠት የሚያስቸግር ቢሆንም፤ የአእምሮ ጤና ማለት የሕይወት ጫናዎችን ተቋቁሞ ፍሬያማ ሕይወት አስተሳሰብና አረዳድ መኖር ነው ካልን፤ የአእምሮ ጤና እክል ማለት ለኑሮ ጫናዎች የምንሰጣቸው ጤናማ ያልሆኑ ምላሾች (maladaptive response) ስብስብ ነው፡፡ ይህም ከማሕበረሰቡ እሴት ወይም የኑሮ ዘይቤ ወጣ ባሉ፣ በግለሰቡ የስራ፣ ማህበራዊ እና አካላዊ ተግባር ላይ አሉታዊ ተጽኖ የሚያመጡ ስሜቶች፣ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች የሚገለጽ ነው፡፡
የአእምሮ ጤና እክል ማለት አስተሳሰባችንን፣ ስሜታችንን እና ድርጊታችንን የሚቀይር የጤና ችግር ማለት ነው፡፡
አዘጋጅ፡ ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ)