እንኳን ደስ ያላችሁ!
መላ የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት የተለያዩ ልዩ-ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን ለሚያሠለጥኑ/ለሚያስተምሩ 50 ባለሞያዎች ሥልጠና ሠጠ።
ሥልጠናውም በነፍስ-ወከፍ ትምህርታዊ ዕቅድ/መርኃ-ግብር (Individualized Educational Plan/Program) በልዩ-ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ባለሞያና መምህር አቶ ፍቅሩ ማሬ ሲሰጥ፤ የሙያዊ ተግባቦትና ሥነ-ምግባር ( Professional Communication and Ethics in Special Education) በልዩ-ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ባለሞያና መምህር ዋኖስ መስፍን ተሠጥቷል።
በቀጣይም ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ እና ተግባር-ተኮር ሥልጠናዎች የሚሠጡ ሲኾን ሥልጠናው ጠቃሚ እንደነበር ሠልጣኞች ገልፀዋል።