የድባቴ ህመም ስርጭቱ
ድባቴ በጣም የተለመደ የአእምሮ ሕመም ከመሆኑ የተነሳ ‹‹የአእምሮ ጤና ጉንፋን›› እስከመባል ደርሷል፡፡ ስንኩልነትን(disability) ከሚያመጡ ህመሞች ቀዳሚዉን ቦታ ይዟል፡፡ በዓለም ላይ ከ200 ሰዎች 25ቹ በዚህ ሕመም የሚታመሙ ሲሆኑ ይህ መጠን ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ስርጭቱ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ላይ በ2 ዕጥፍ ከፍ ይላል፡፡ በየትኛውም የእድሜ ክልል ሊከሰት የሚችል ቢሆንም በአማካይ 40ዓመት ላይ በብዛት ይከሰታል፡፡ ጥናቶች ያላገቡ፣ የፈቱ ወይም አጋራቸው የሞተባቸው ሰዎች ላይ የመከሰት እድሉ ከፍ ያለ እንደሆነ ነገር ግን ከሀብት እና ድህነት ጋር ተያያዝነት እንደሌለው ያሳያሉ፡፡ ምንም እንኳን አስጨናቂ ሕመም ቢሆንም እና ዉጤታማ ህክምና ቢኖረውም፤ ህመምተኛው መገለልን በመፍራት ወይም በሌላ ምክንያት ሊደብቀውና በመጨረሻም ሕመምተኛው ራሱን አጥፍቶ ሊገኝ ይችላል፡፡
መንስኤዎው
እንደማንኛውም የአእምሮ ሕመም የድባቴ ህመም በተላያዩ ስነ–ሕይታዊ፣ ማሕባራዊ እና ስነ–ልቦናዊ ምከንያቶች ሊነሳ ይችላል፡፡
ስነ ሕይታዊ (biological)
- በዘር
- በአእምሮ ዉስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች (Neurochemicals) መዛባት
- በአንጎል አካላዊ ቦታዎች ላይ የሚያጋጥሙ ጉዳቶች
- አንዳንድ የአንጎል ክፍሎች ከሚገባው በላይ ንቁ መሆን (Neurochemical)
ስነ ማሕባራዊ (Social) እና ስነ–ልቦናዊ ምከንያቶች (Psychological)
- አድካሚ የህይወት ዉጣ ዉረዶች
- ከ11ዓመት እድሜ በፊት ወላጆችን ማጣት
- የስብዕና አይነቶች
- የግንዛቤ መፋለሶች
ለረጅም ግዜ ከመጥፎ የህይወት አጋጣሚዎች የሚያድነን/የሚያወጣን አካል ስናጣ እና ከዚህ ህይወት መውጣት እንደማንችል በመረዳት ተስፋ ስንቆርጥ