Skip to content
Email Telegram Linkedin Facebook YouTube
WeMind Ethiopia
  • Home
  • Info & GuidanceExpand
    • Videos
    • Where to go
    • Mental Wellbeing
    • Sign and Symptoms
    • Conditions
    • Treatments
    • Emergencies
    • Frequently asked questions
    • Support Groups
  • storiesExpand
    • Submit story
  • Advocacy
  • EventsExpand
    • Upcoming Events
    • Add/Edit Events
    • Manage events
  • MoreExpand
    • Services
    • About
    • Contact
Contact Us
WeMind Ethiopia

ሲሲሊያ ሚክጎው

የስነ ፈለክ ተማራማሪ ናት፡፡ ፐልሳር የሚባል ግኝት አግኝታለች፡፡ በዚህም የPenn State Pulsar Search Collaboratory መስራች እና ፕሬዝዳንት ናት፡፡ ሲሲሊያ በምርምሩ ባስመዘገበችው ስኬት ጎን ለጎን ከHallucination ጋር ትታገል ነበር፡፡ አሁን የዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን የሚረዳ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት መስርታ ተማሪዎችን ትረዳለች፡፡ በዓለም አቀፍ መድረኮችም ስለ አእምሮ ጤና ጥብቅና ትቆማለች፡፡

የንግግሩን አማርኛው ትርጉም ለማንበብ

በTEDx ላይ ያደረገችው ንግግር ለመከታተል

ከንግግሯ የተወሰዱ

• ሲሲሊያ ሚክጎው እባላለሁ፡፡ አስትሮኖመርና አስተርፊዚስት ነኝ የፐልሳር ግኝትን አግኝቻለሁ፡፡
• ያልተናገርኩት ምስጢር ግን ነበረኝ – ስኪዞፍሬኒያ፡፡
• እናቴን ደውዬ ሀኪም ማነጋገር አለብኝ ስላት መልሷ አይሆንም ለማንም መናገር አትችይም፡፡  ይህ በእኛ የህክምና ታሪክ ውስጥ ሊካተት አይችልም፡፡ ….እህቶችሽን አስቢ….ሥራ ማግኘት አትችይም የሚል ነበር
• የሕክምና ዕርዳታ ለማግኘት የወሰንኩት ውሳኔ እስካሁን ከወሰኳቸው ውሳኔ ሁሉ የላቀው ነው።
• ተገቢውን የህክምና እርዳታ ባላገኝ ኖሮ ዛሬ በፊታቸሁ አልቆምም ነበር።
• ማንም የህክምና እርዳታ እንዳታገኙ እንዲያሳምናቹህ አትፍቀዱ። አይበጅም! ምርጫችሁ ነው፣ መብታቹህም ነው።”
• ስሜ ሴሲሊያ ሚክጎው እባላለሁ፣ ስኪዞፈሪንያ አለብኝ እና ጭራቅ ግን አይደለሁም።

ሰላም፣ ስሜ ሲሲሊያ ሚክጎው እባላለሁ። እኔ እዚህ ፔን ግዛት ውስጥ የአስትሮኖመር እና አስተሮፊዚክስ ተመራማሪ ነኝ፣ እና Penn State Pulsar Search Collaboratory መስራች እና ፕሬዝዳንት ነኝ ። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ፣ በPulsar Search Collaboratory አማካኝነት Pulsarን ከሌሎች ጋራ በማግኘቴ እድለኛ ነኝ ። ፑልሳር የዲፖል ኤሌክትሮማግኔቲክ ጨረር የሚያመነጭ እጅግ በጣም ጥቅጥቅ ያለ የኒውትሮን ኮከብ ነው። በመሠረቱ፣ ከፀሀያችን በጣም የሚበልጥ፣ ጥቅጥቅ ያለ እምብርት ትቶ፤ የውጪውን ንብርብሩን እያነፈሰ የሚሄድ፣ ከፀሀያችን በጣም የሚበልጥ ኮከብ አስቡ። ይህ ግኝት ዩናይትድ ስቴትስን ወክዬ በሩሲያ ውስጥ በአለም አቀፍ የህዋ ኦሊምፒክ ላይ እንድወዳደር በር ከፈተልኝ። በተጨማሪም፤ የቨርጂኒያ ኤሮስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ምሁር እንድሆን፡፡ ምን እያሰባችሁ እንዳላችሁ አውቃለሁ
“ምኗ ጀግና ናት!”
“ብርቱ ጀግና!”
 
መልካም፣ ለረጅም ጊዜ ይህ ጀግንነት ሚስጥር ነበረው፡፡ ለማንም ለመናገር በጣም የፈራሁበት እና የተሸማቀኩበት ምስጢር። ያም ምስጢር ስኪዞፈሪንያ እንዳለብኝ ነው። ግን ስኪዞፈሪንያ ምንድን ነው? ስኪዞፈሪንያን የህመሞች ጃንጥላ አይነት ምርመራ አድርጎ ማሰብ አስፈላጊ ነው። NAMI ዴሉዥን እና ሃሉሲኔሺን የመሳሰሉትን ዋና ዋና ምልክቶች ስኪዞፈሪንያ ለመመርመር በሚያስችሉ መንገዶች መሆናቸውን ያሳያል። ነገር ግን አንድ ሰው ዴሉዥን ወይ ሀሉሲኔሺን ሳይኖረው ስኪዞፍሬኒያ ሊኖረው እንደሚችል ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ከስኪዞፈሪንያ ጋር ያለው ታሪክ ለየራሱ ልዩ ነው። ዛሬ ስለ ስኪዞፈሪንያ ያለኝን ታሪክ እናገራለሁ ።
 
በሕይወቴ ሙሉ ስኪዞፈሪንያ እንዳለብኝ ይታሰብ ነበር። ነገር ግን በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በጣም አይሎብኝ ነበር፡፡ እና ኮሌጅ ውሰጥ ደግሞ ባሰ፡፡ በየካቲት፤ (ፍሬሽ ተማሪ እያለሁ) የራሴን ሕይወት ለማጥፋት ከሞከርኩኝ ወዲህ ሕይወቴ ተቀየረ “እንዴት?” ብላችሁ ትጠይቁኝ ይሆናል። ምክንያቱም ህይወቴ የቁም ቅዠት ሆኖብኝ ነበር። የሚከተሉት ምስሎች ለኔ በጣም ቀስቃሽ ስለሆኑ Microsoft artistic effectsን በመጠቀም አስተካክያቸው ነው። በዚህ ጊዜ hallucinate ማድረግ ጀመርኩ (ለሌሎች የማይታዩ ነገሮችን ማየት፣ ሌሎች የማይሰሟቸው ነገሮችን መስማት፣ ሌሎች የማያሸቱትን ማሽተት…)። የሌሉ ነገሮችን ማየት፣ መስማት ጀመርኩ።
 በሄድኩበት ቦታ ሁሉ የእስጢፋኖስ ኪንግን “IT” ከሚለው ፊልም ጋር ተመሳሳይ የሆነ “ቀልደኛ” ይከተለኝ ነበር። በሄድኩበት ቦታ ሁሉ እሱ እያላገጠብኝ፣ እየሳቀ፣ እየደበደበኝ፣ አልፎ አልፎም እየነከሰኝ ይከታተለኝ ነበር።
አንዳንዴ ደግሞ ሸረሪቶችን (አንዳንዴም በጣም ትንንሽ ሸረሪቶችን) አያለሁ፡፡ በእርግጥ በእውነተኛው አለም ውስጥ ትንንሽ ሸረሪቶችን ልናይ እንችላለን፡፡

ስለዚህ በዚህ ወቅት የምር የእውነት ሸረሪቶችን እያየሁ ወይስ hallucinate እያደረኩ እንደሆነ ለመለየት እቸገራለሁ። መቼ ሀሉሲኔት እንደማደር መለየት ላይ በጣም ጎበዝ ነኝ እና መነሻውም በጭንቅላቴ ውስጥ የኬሚካል አለመመጣጠን እንደሆነ አውቃለሁ። እነዚህን ሀሉሲኔሽኖች ስም እንኳ አልሰጣም። ግዙፍ ሸረሪቶችንም አያለሁ። በተለይ አንድ ሸረሪት በጣም አስታውሰዋለሁ፡፡ ትልቅ ነው፣ ቆዳማ ቆዳ አለው፣ ጥቋቁር እግሮች እና ቢጫ ሰውነት አለው። አንድም ድምፅ ከአፉ አይወጣም። ነገር ግን እግሮቹን ሲያንቀሳቅስ የእግሮቹ ኮቴ የሚወጣው ድምጽ ልክ የህጻን ልጆች ሳቅ ይመስላል። በጣም እረበሽበታለሁ፡፡ ከሁሉም ግን ይህችን ሴትዮ ማየት ስጀምር የማልታገሰው መረበሽ ውስጥ ገባሁ፡፡ “the ring” የሚለው ፊልም ውስጥ እንዳለችው ናት፡፡

የምታውራው ከራሷ ጋር ነው፡፡ እኔን ለማስጨነቅ ምን በምን ጊዜ ማለት እንዳለባት ታውቃለች፡፡  ከሁሉ የከፋው ግን ቢላዋ ይዛ ትዞራለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፊቴን ትወጋኝ ነበር። በዚህም ኮሌጅ በነበርኩበት ጊዜ ፈተናዎችን፣ ጥያቄዎችን እና የቤት ስራዎችን እንዳልሰራ አድርጋኝ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ወረቀት እንኳን ማየት አልችልም ምክንያቱም የማያቸው ነገሮች በእኔና በማነበው መጽሐፍ መሀል እየሆኑ እይታዬን ይጋርዱኛል፡፡ ስለ ሀሉሲኔሽኔ ብዙ ጊዜ በግልጽ አልናገርም ምክንያቱም ሰዎች የማየውን ከነገርኳቸው በኋላ በፍርሃት ይመለከቱኛል። ከሌሎቻችሁ ብዙም የተለየ አይደለሁም። ሁላችንም ተኝተን ስንቓዥ ነገሮችን እናያለን፣ እንሰማለን፣ እንዳስሳለን። ለየት የሚለው፣ እኔ ከእንቅልፌ ነቅቼም ቢሆን ቅዠቶቼን ማጥፋት የማልችል ሰው መሆኔ ነው፡፡  ከ4 ዓመታት በላይ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበርኩ።

አሁን የማየውን ነገር እንዳላየሁ በማስመሰል ጎበዝ ሁኛለሁ። ይሁን እንጅ የሚቀሰቅሱብኝ ነገሮች አሉኝ፡፡  ለምሳሌ ቀይ ቀለም ማየት ለእኔ በጣም ቀስቃሽ ነው፡፡ እናንተ ይህንን አስተውላችሁ እንደሆነ አላውቅም ግን የቆምኩበትን ምንጣፍ ቀይረውብኛል።  ከቀይ ወደ ጥቁር ምንጣፍ ቀየሩት። በህይወቴ ልክ እንደ ቀልድ እስቃለሁ፤ ምክንያቱም፤ የሚያስቸግሩኝ ብቸኛው የቀለም ጥምረት ቀይ እና ነጭ ነው። የ TED ቀለሞች ምንድ ናቸው? (ሳቅ) በእውነት ሰዎች! በነዚህ ቀለሞች ላይ ችግሮች አሉብኝ፡፡ ምክንያቱም  የሚከታተሉኝ ‹‹ቀልደኞች›› ቀለማቸው ቀይ ፀጉር እና ነጭ ቆዳ ያላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ እነርሱን ችላ ልላቸው የምችለው ወደ እነርሱ ባለመመልከት ነው፡፡ ነገር ግን ደማቅ ቀይ እና ነጭ ቀለማት እስካሉ ድረስ አብረውኝ እንዳሉ አውቃለሁ። ግን እያየኋቸው እንደሆነ እናንተ አታውቁም።

‹‹ቀልደኛው›› ዛሬ በታዳሚው ውስጥ አለ፡፡ እናንተ ግን አታዩትም። እስኪ ከእናነተ መሐል ኦስካር ሽልማትን የሚጠብቅ? እጅ ወደ ላይ! እናንተ ሰዎች ፍላጎት እንደሚኖራችሁ አውቅ ነበር! ደህና፣ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ‹‹ኖርማል›› እየመሰሉ ለሚያስመስሉ ለሽማት ቢታጩ ኖሮ፣ ስኪዞፈሪንያ ያለባቸው ሰዎችም በእጩነት ይመረጡ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ስኪዞፈሪንያ እንዳለብኝ ስናገር፣ ለእኔ በጣም ቅርብ ለሆኑ ሰዎች እንኳን አስደንጋጭ ነበር። ራስን የማጥፋት ሙከራ ካደረግኩ በኋላ የሚያስፈልገኝን ሕክምና ለማግኘት ስምንት ወራት ፈጅቶብኛል። የስኪዞፍሪንያ ምርመራ እንኳ አላደረኩም።  የህክምና እርዳታ እንዳላገኝ የከለከሉኝ እንደዚህ አይነት ንግግሮች ናቸው። ከእናቴ ጋር በስልክ ያደረኩትን ንግግር አስታውሳለሁ፡፡


“አይ, አይ, አይሆንም, አይሆንም፡፡ ስለዚህ ለማንም መናገር አትችይም፡፡  ይህ በእኛ የህክምና ታሪክ ውስጥ ሊካተት አይችልም፡፡ ስለ እህቶችሽ አስቢ, የእህቶችሽን የወደፊት እጣ ፈንታ አስቢ፡፡  ሰዎች እብድ እንደሆንሽ ያስባሉ፡፡  አደገኛ እንደሆንሽ አድርገው ያስባሉ እና ሥራ ማግኘት አትችይም።
አንድ ምሽት ራሴን ሆስፒታል ወስጄ ማስፈተሸ እንዳለብኝ ተገነዘብኩ፡፡ ምክንያቱም በመድኃኒቴ ላይ አንዳንድ ለውጦች ያስፈልጉኝ ነበር። እናም እራሴን ወደ ድንገተኛ ክፍል አስገባሁ፡፡ ሀኪሞቹን አነጋገርኳቸው፡- “እሺ፣ መድሃኒቶቹን እናስተካክል፣ እዚህ ማደር ትችያለሽሽ አሉኝ። ሁሉም ጥሩ ነበር። ከአጭር የአንድ ሌሊት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ፣ እዚህ ፔን ግዛት ወደሚገኘው ዶርሜ ተመለስኩ፣ የዶርም ጓደኞቼ በጣም እንደተጨነቁ ይለያል፡፡ ምን እንደሚያሳስባቸው ይገባኛል – በነሱ ቦታ ብሆን እኔም ያሳስበኝ ነበር ። ሁላችንም ተነጋገርን እና ሌላ የሆስፒታል ቆይታ እንደሚያስፈልገኝ ወሰንን።  ለመሄድ ዝግጅት ላይ ነበርኩ፣ ፈፅሞ እምቢ አላልኩም፣ ለመሄድ ፈቃደኛ ነበርኩ። ነገር ግን ቀጥሎ የሆነው ነገር ይቅር የሚባል አልነበረም።


ፖሊሶችን ወደ ዶርሜ አመጡብኝ፡፡ አብረውኝ ከሚኖሩ ጓደኞቼ ፊት ለፊት፣ ከለበሱኝ እና እጄን እንዳታስቀምጡኝ ማሳመን ነበረብኝ። ከዚያም አመጡኝ፡፡ በዶርም ጓደኞቼ ፊት በጉልበት በደረቴ ደፍተው ያዙኝ፡፡ የእጅ ካቴና እንዳያደርጉብኝ ማሳመን ነበረብኝ፡፡ ከዚያን ሬዲፈር አጠገብ በመንገድ ላይ የቆመ የፖሊስ መኪና ውስጥ አስገቡኝ። ጓደኞቼ ይህንን ትርዒ ይመለከቱ ነበር፡፡ ታክሜ ስመለስ ነገሮች ተቀያይረው ነበር፡፡ ሰዎች የሆነ ነገር እንደተቀየረ ስለሚያውቁ ታሪኩን ማስተካከል ነበረብኝ። ስለዚህ ስለስኪዞፈሪንያዬ በብሎግ ከፈትኩኝ፡፡ ሁሉንም የብሎግ ጽሁፎቼን በፌስቡክ ላይ አወጣኋቸው። እዚያ ያገኘሁት ድጋፍ በጣም አስገርሞኝ ነበር፡፡ እንደ እኔ በጣም ብዙ ሌሎች ሰዎች እንዳሉም ተገነዘብኩ። በእውነቱ በጣም ተገረምኩ! ጥቂት ጓደኞቼ ስኪዞፈሪንያ እንዳለባቸው ገለጹልኝ። አሁን የአእምሮ ጤና ጠበቃ ለመሆን ቆሚያለሁ፡፡ በምርመራዬ ለራሴ በማዘን አልዋሽም። ይልቁንም፣ እኔ እንደ አንድ የጋራ መለያ ልጠቀምበት እፈልጋለሁ፣ ስለዚህ ሌሎች ስኪዞፈሪንያ ያለባቸውን ሰዎችን መርዳት እችላለሁ። እና በዓለም ዙሪያ ስኪዞፈሪንያ ያለበት ማንኛውም ሰው “schizophrenia አለብኝ” የሚለውን ቃል ለመናገር መፍራት እስካላቆመ ድረስ እረፍት አላደርግም። ምክንያቱም ስኪዞፈሪንያ መኖሩ ምንም ችግር የለውም፣ በእርግጥም የለውም፡፡ ምክንያቱም 1.1 %  የሆነው ከ18 ዓመት በላይ የሆነው የአለም ህዝብ ስኪዞፈሪንያ አለበት። ይህም በዓለም ዙሪያ 51 ሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች እና 2.4 በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ብቻ 51 ሚሊዮን ሰዎች ማለት ነው፡፡


በአእምሮ ጤና ማህበረሰብ ውስጥ እንኳን ስኪዞፈሪንያ ያለበት ሰው ይገለላል ምክንያቱም ሰዎች “ምቾት እንዲሰማቸው” ስለማያደርግ ነው። ለዚህም ነው ለትርፍ ያልተቋቋመ “Students with Schizophrenia” የሚባል ድርጅት ያቋቋምኩት፡፡ የኮሌጅ ተማሪዎችን የምናበረታታበት እና የሚያስፈልጋቸውን ግብአት የምናገኝበት፣ በኮሌጅ እንዲቆዩ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የምናደርግበት። ምክንያቱም ስኪዞፍሬኒያ ይዟችሁም ውጤታማ መሆን ይቻላል። የስኪዞፈሪንያ ገጽታን መለወጥ ያስፈልገናል፡፡ ምክንያቱም ስለዙ የሚባለው የተሳሳተ ግንዛቤ ነው፡፡
 
ማንም ሰው የአእምሮ ሕመም ኖሮብህ  የአዕምሮ ጥንካሬ እንደሌለህ እንዲነግርህ አትፍቀድ። አንተ ጠንካራ ነህ፣ ጎበዝ ነህ ፣ ተዋጊ ነህ። እንደ አለመታደል ሆኖ ይህ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ለአንዳንዶች በጣም ዘግይቷል። ስኪዞፈሪንያ እንዳለብኝ ካደረኩ በኋላ እዚህ ፔን ስቴት ውስጥ ወደ ተለያዩ የመማሪያ ክፍሎች እንድመጣ ተጠየቅኩኝ፣ እና ስለስኪዞፈሪንያ ስላጋጠመኝ ልምዴን ነገርኳቸው። አንድ ክፍል በተለይ ጎልቶ ታይቶ ነበር፡፡በፊት አንዷ ስኪዞፈሪንያ እንዳለባት ለክፍል ተናገራ ነበር። በጀግንነቷ አመሰግኛት ነበር። ሆኖም ገን እኔ መጥቼ ያንን ክፍል ሳናግረው እራሷን አጥፍታለች። ለእሷ በጣም ዘገየን። ለእሷ በጣም አርፍጄ ነበር። እዚህ በፔን ስቴት ግዣት ውስጥ ለዓለም ምሳሌ መሆን አለብን፡፡ ምክንያቱም ይህ በፔን ስቴት ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ እየሆነ ያለ ነገር ነው። እዚህ በፔን ግዛት ለተማሪዎቻችን ከጎናቸው እንደሆንንነ, ስለ አእምሮ ጤንነት እየተነጋገርን እንደሆነ፤ እና ስለ ስኪዞፈሪንያ ለመናገር አንደማንፈራ ማሳየት አለብን፡፡
 

ስሜ ሴሲሊያ ሚክጎው እባላለሁ፣ ስኪዞፈሪንያ አለብኝ እና ጭራቅ ግን አይደለሁም።

Special books by special kids ጋር ያደረገችው ቃለ መጠይቅ (2017)

በ2020 እዚሁ መድረክ ላይ ያደረገችው ቃለ መጠይቅ

ከ5 ወራት በፊት ያደረገኝው ቃለ መጠይቅ

Hakim Ethiopia

Ethiopian blend of Medicine, History and Humor

Addis Ababa, Ethiopia

Events Board

  • All Events
  • Workshops and Trainings
  • Support Groups
  • Wellness Retreats
  • Health Fairs

Useful Links

  • Give
  • Contacts
  • Privacy Policy
  • Services
  • Our Beliefs

Let those who cannot pay for medical bills not be left behind.

© 2025 WeMind Ethiopia, powered by Nexterize Solutions

error: Content is protected !!
Scroll to top
  • Home
  • Info & Guidance
    • Videos
    • Where to go
    • Mental Wellbeing
    • Sign and Symptoms
    • Conditions
    • Treatments
    • Emergencies
    • Frequently asked questions
    • Support Groups
  • stories
    • Submit story
  • Advocacy
  • Events
    • Upcoming Events
    • Add/Edit Events
    • Manage events
  • More
    • Services
    • About
    • Contact
Facebook X Instagram
Contact Us
Search