የማግለል ይዘቶች
ህዝባዊ ማግለል (public stigma): ማህበረሰቡ ታማሚው ላይ የሚያሳየው ማግለል ሲሆን ለታካሚው ከሚሰጠው ያልተስተካከለ አመለካከት እስከ ግልጽ አድሎ (ለምሳሌ ስራ መከልከል) ሊደርስ ይችላል
የታሰበ መገለል (Anticipated stigma): ታማሚው የጤናው ሁኔታ ከታወቀ መገለል እንደሚደርስበት ያስባል
ከስያሜ መሸሽ (label avoidance)፡ የአእምሮ ታማሚ ነው ላለባል በመፍራት ይህንን ስያሜ ያሰጠኛል ከሚለው አከባቢዎችና አገልግሎቶች (ሀኪም ቤቶች፣ የማገገሚያ ቦታዎ፣ የስነ ልቦና አገልግሎት ቦታዎች…) ራሱን ያርቃል፡፡ ይህም የህክምና እርዳታ በጊዜ እንዳያገኝ፥ ህክምና ጀምሮ ከሆነም እንዲያቋርጠው ያደርገዋል፡፡
ራስን ማግለል (self-stigma)፡ በማህበረሰቡ የሚንጸባረቁት ትክክል ያልሆኑን አመለካከቶች ትክክል አድርጎ መቀበል ሲጀምር እና አስተሳሰቡን ወደራሱ ማስረጽ ሲጀምር ነው፡፡
አንድ በግ ተሸክሞ ይሄድ የነበረን ሰው ሌቦች መንገድ ላይ ያገኙት በጉን መውሰድ ፈለጉ፡፡ በመንገድ ተደብቆ አንዱ “ምን ሆነህ ነው ውሻ ተሸክመህ የምትሄደው” ይለዋል፡፡ ትንሽ ራቅ ብሎ ሌኛው ይህንኑ ይደግምለታል፡፡ ሰውየው መጠራጠር ይጀምራል፡፡ አሁንም ራቅ ብሎ ሌላኛው ይህነኑ ሲደግምለት በጉን ትቶት ሄደ እንደሚባለው፡፡ በተለይ በህመሙ ጊዜ እንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል፡፡
የዝምድና መገለል (associative stigma)፡ ይህ በታማሚው ቤተሰብ፣ ዘመዶች ወይም የጤና አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የሚደርሰው መገለል ነው፡፡ በዚህም ተጽኖ ምክንያት ቤተሰብ ወይም ጓደኞች ታማሚውን ህመሙን በምስጢር እንዲይዝ ወይም ህክምናውን እንዲያቋርጥ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ ልክ እንደ ታማሚ ቤተሰብና ጓደኛም ሀፍረትና የተዛቡ አመለካከቶችን ወደ ውስጣቸው ሊያሰርጹት ይችላሉ፡፡ ሌላው፣ ቤተሰቦች (እንርሱ ላይ ባይደርስባቸውም) በልጃው ላይ በሚደሰው መገለል ምክንያት መጎዳት፣ ቁጭት፣ ተስፋ መቁረጥ እና መጠቃት ሊሰማቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ እናት በልጇ ላይ የሚደርሰው “ብሽሽቅ” ልቧን ሊሰብራት ይችላል፡፡
