ፍሬ ሀሳብ
ሀሉሲኔሽን ማለት ድምጽ ሳይኖር ድምጽ መስማት፣ የሚታይ ነገር ሳይኖር ማየት፣ የሚሸት ነገር ሳይኖር ማሽተት፣ ንክኪ ሳይኖር እንደተነኩ መሰማት ነው፡፡
- አይነቶች
- የድምጽ ሀሉሲኔሽን፡ ድምጽ ሳይኖር የሆነ ነገር መስማት፡፡ ለምሳሌ ሰው ሳይጠራን ሰው ስማችንን እንደጠራን መስማት፡፡
- ራዕይ (የእይታ ሀሉሲኔሽን)፡- የሚታይ ነገር ሳይኖር የሆነ ነገር ሲታየን
- የሽታ ሀሉሲኔሽን፡ የሚሸት ነገር ሳይኖር ሽታ ሲሸተን
- የንክኪ ሀሉሲኔሽን፡- ምንም ነገር ሳይነከን እንደተነካን ሲሰማማ
- የሀሉሲኔሽን መንስኤዎች
- የአእምሮ ሕመም እና ውጥረት
- ጥቆማ
- የስሜት ህዋስ አካላት ችግር
- የአንጎል ህመም
✧ ✧ ✧ ✧ ✧ ✧
ሀሉሲኔሽ ማለት የሚታይ ነገር ሳይኖር የሆነ ነገር ስናይ፣ ድምጽ የሚያወጣ ነገር ሳይኖር ድምጽ ሲሰማን፣ የሚሸት ነገር ሳይኖር ስናሸት…. ማለት ነው፡፡ ድምጽን እንደምሳሌ ብንወስድ፣ የሚሰማን ድምጽ ትክክለኛ ከሆነ አካል እንደተላለፈ ቢሰማንም ነገር ግን ወደ ጆሮአችን የገባ ምንም አይነት ድምጽ የለም፡፡ በዚህም ድምጹ በአከባቢያችን ላሉ ሰዎች አይሰማቸውም፡፡ ይህ የገጠመው ሰው ድምጹ ከ‹‹ውስጥ›› ሳይሆን ከ‹‹‹ውጭ›› እንደመጣ ነው የሚረዳው፡፡ ድምጹ ከውጭ መጥቶ ሳይሆን ከራሴ የሚወጣ ነው ብሎ ካሰበ ሃሉሲኔሽን አይባልም- ይህኛው ክስተት ‘pseudo-hallucination’ ይባላል፡፡ (ይስሙላ ሀሉሺኔሽን ብለን እንተርጉመው?)
የሀሉሲኔሽን አይነቶች
ድምጽ መስማት (የድምጽ ሀሉሲኔሽን )/ Auditory hallucination
የደምጽ ሀሉሲኖሽኖች ስኪዞፍሬኒያ፣ የመርሳት ህመሞች፣ ድባቴ፣ ባይፖላር እና በመሳሰሉት የአእምሮ ሕመሞች ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ድምጾቹ ጫጫታዎች ወይም ፉጨት ወይም የደውል ድምጽ ወይም ንግግር ወይም ሙዚቃ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ድምጾች ግልጽ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ እና ግልጽ ያልሆኑ እና በህመምተኛው በምንም መልኩ ሊገለጹ የማይችሉ ናቸው። ብዙውን ጊዜ ታካሚዎች ድምጾቹ የሚመጡበትን አቅጣጫ ወይም የተናጋሪውን ጾታ ለመግለጽ ባለመቻላቸው ይረበሻሉ፡፡ ድምጾቹ አንዳንድ ጊዜ ለታካሚው ትዕዛዞችን ይሰጣሉ; እነዚህ ‘አስገዳጅ ሀሉሲኔሽን’ ይባላሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች፤ ድምጾቹ ለሶስተኛ ወገን ስለሰውየው አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ለራሱ ለታካሚው አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ የድምጽ ሀሉሲኔሽኖች ተሳዳቢ፣ ገለልተኛ ወይም አጽናኝ ሊሆኑ ይችላሉ።
በታካሚ ላይ ያላቸው ተጽኖ የተለያየ ነው፡፡ ብዙ ሕመምተኞች ሀሉሲኔት እያደረጉ ነገር ግን እንዳላደረጉ ማስመሰል ይችላሉ። ሌሎች ከማዳመጥ አልፎ ተርፎም አንዳንድ ጊዜ ምላሽ ሲሰጡ ወይም ሲታዘዙ ይስተዋላል፡፡
በጀርመንኛ Gedankenlautwerden በመባል የሚታወቀው የሀሉስኔሽን አይነት ላይ አንድ ሰው ራሱ የሚያስባቸውን ሀሰቦች ከውጭ እንደተወሩ ሁነው ይሰማዋል፡፡ የእንግሊዘኛ ቃል ‘thought echo’ ይለዋል (የሀሰባብ ማሚቶ እንበለው በአማረኛ?)
ታካሚዎች የድምጾቹን አመጣጥ በተመለከተ የተለያዩ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ድምጾቹ የጥንቆላ፣ የቴሌፓቲ፣ የሬዲዮ፣ የቴሌቭዥን እና የመሳሰሉት ውጤቶች ናቸው ብለው አጥብቀው ይከራከሩ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ድምጾቹ ከሰውነታቸው ውስጥ (እንደ ክንዳቸው፣ እግራቸው፣ ሆዳቸው ወዘተ) እንደሚመጡ ይናገራሉ።
ጥቂት ሕመምተኞች ድምጽ መስማታቸውን ይክዳሉ፡፡ ነገር ግን ሰዎች ስለእነሱ እያወሩ እንደሆነ ይናገራሉ። ድምጾቹ ብዙውን ጊዜ ተሳዳቢዎች ስለሚሆኑ ታካሚው ተጠያቂ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን ሰዎች ሊያጠቃ ይችላል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የምትሆነው ለብዙ አመታት ተኝታ ታካሚ የነበረች ግሪካዊት ሴት። ሁልጊዜ ድምጽን መስማት ትክዳለች ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ በባልንጀሮቿ ላይ ጥቃት ትፈጽማለች። አንድ ቀን ግሪክኛ የሚናገር ሰው እንዲጠይቃት ትፈልግ እንደሆነ ተጠየቀች። በሆስፒታሉ ውስጥ ያሉ ሁሉም ሰዎች ግሪክኛ ስለሚናገሩ ይህ አስፈላጊ እንዳልሆነ ተናገረች። በግሪክኛ ለእውነተኛ ሰዎች የተናገረቻቸው ተከታታይ ድምጾች እንደሰማች እና ምክንያት የሌላቸው የሚመስሉ ጥቃቶቿም በዚህ ተገፋፍተው እንደነበር ግልጽ ሆነ።
ራዕይ (visual hallucination)
የሚታዩት ነገሮች ብርሀን ጭላንጭል ወይም ሰዎች፣ ነገሮች ወይም እንስሳት ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ ታካሚ ለበረራ ሲሳፈሩ ሻንጣቸውን በጀርባቸው የያዙ አይጦችን አየሁ በሏል። የሲስሊያ ሚክሆው ልምድ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ ሲሲሊያ ‹‹ቀልደኛውን›› ሸረሪቶችን፣ የምታስፈራውን ሴትዮ እንደምታይ ተናግራለች፡፡ የሚጥል በሽታ ያለባች ሰዎች እነዚህ ክስተቶች ይፈጠራሉ፡፡
የሽታ ሀሉሲኔሽን (olfactory Hallucinations (OH))
በቅዱስ አማኔእል ሆሰፒታል አንድ ታካሚ ይህንን ክስተት እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ ‹‹አንዳንዴ ከየት እንደመጣ የማላውቀው ጥሩ ሽታ ይከበኛል፡፡ በሌላ ጊዜ በጣም አስቀያሚ ሽታ ይሸተኛል፡፡ ይህ ሺታ ልቋቋመቸው የማልችለው አይነት ነው፡፡ ምን እንደማደርግ ይቸግረኛል፡፡ አፍንጫዬን የፈለገ ጥርቅም አድርጌ ብዘጋውም ሽታውን አለማሽተት አልችልም፡፡ ከሱ በምንም አላመልጥም፡፡››
ምንም ሽታ በሌለበት ቦታ ሽታ ማሽተት ነው፡፡
የጣዕም ሀሉሲኔሽን
ይህ ሀሉሲኔሽን ከትክክለኛው የጣዕም ግንዛቤ ለመለየት የሚከብድ ነው፡፡ አንድ ሰው ምንም ሳይቀምስ የሆነ ጣዕም የሚያጣጥም ከሆነ ሀሉሲኔት እያደረገ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዴሉዥንም ለመለየት አስቸጋሪ ናቸው፡፡
የንክኪ (የመዳሰስ) ሀሉሲኔሽን / Tactile Hallucinations
ይህ ምልክት ሰውነታችን ላይ ምንም ንክኪ ሳይደረግ እንስሳት እንደሄዱብን፣ ነፋስ እንደነፈሰብን፣ ሙቀት እንዳገኘን እንዲሁም ለወሲብ የሚቀሰቅሱ ንኪኪዎችን እንደተነጋን የሚሰማን ሀሉሲኔሽን ነው፡፡ ለረጅም ጊዜ በብዙ ሲጠጡ የነበሩ ሰዎች ድንገት የመጠጥ ልምዳቸውን ቢያቋርጡት በሰውነታቸው ላይ የሆነ ተባይ እየሄደ እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ ኮኬን የተጠቀሙ ሰዎችም አንዲሁ፡፡ በሰውነታቸው ውስጥ የሆነ እንስሳ እየተራወጠ የሚመስለቸውም አሉ፡፡ ሰውነታቸው ወይም የአካል ክፍላቸው እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ፣ እየተጣመመ እንደሆነ ወይም ተንቅሎ እንደሄደ የሚሰማቸውም አሉ፡፡
የሀሉሲኔሽን መንስኤዎች
ሀሉሲኔሽን የአእምሮ ሕመሞች፤ የጥቆማዎች፤ የስሜት ህዋሳት መዛባ፤, የስሜት መረበሽ እና የማዕከላዊው የነርቭ ሥርዓት መዛባት ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡
የአእምሮ ሕመም
በጣም የተጨነቁ፣ የጥፋተኝነት ስሜት ያላቸው ታካሚዎች እነሱን የሚነቅፉ ድምፆች ሊሰሙ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፣ ስኪዞፈሪንያ ያለበት ሰው ስለ እርሱ አስተያየት የሚሰጡ (ሀሜታሞች እንበላቸው?)፣ ትዕዛት የሚሰጡ፣ የሚሳደቡ ወይም የሚያጽናኑ ድምጦችን ሊሰማ ይችላል፡፡
ጥቆማ
ብዙ ሙከራዎች እንደሚያሳዩት አንድን ሰው ሀሉሲኔት እንዲያደርግ ማሳመን ይችላል፡፡ አንድ ጥናት ላይ እኩል የብርሀን መጠን በሚበራባቸው ኮሪደሮች መሀል እንዲያልፉ ተደረጉ፡፡ የሆነ ኮሪደር ጋር የደበዘዘ ብርሀን እንዳለና እዛ ቦታ ሲደርሱ እንዲቆሙ ለተሳታፊዎቹ ተነገራቸው፡፡ ብዙዎቹ ተሳታፊዎች አንድ ቦታ ሲደርሱ ቁመዋል። ሂፕኖሲስ በሚባል ዘዴ አንድን ሰው ሀሉሲኔት ማድረግ እንዲችል ማድረግ ይቻላል።
የስሜት መቀበያ አካሎች መታመም
አይናችን ከታመመ የማይታይ ነገር ሊታይ ይችላል፡፡ ጆሮ ከታመመም ያልተፈጠረ ድምጽ ሊሰማን ይችላል፡፡ ለምሳሌ፣ የ66 ዓመቷ በግላኮማ የተጠቃች ሴት ለሌላ ሰው የማይሰሙና የማይታዩ ነገሮችን አየሁ ስትል ነበር። አንዲት ማየት የማትችል ሴት (አይነስውር) ድግሞ ከሆነ ጊዜ በኋላ ነገሮችን አየሁ ስትል ነበር፡፡
የአንጎል ህመም
የዲኤንሴፋሎን እና የኮርቴክስ በሚባሉ የአንጎል ክፍሎች ላይ ቁስል በሚኖርበት ጊዜ ታካሚው ለሌላ ሰው የማይታዩ ነገሮች ሊታዩት ይችላሉ፡፡
ይህ ምልክት ካለበዎ ሀኪም ያማክሩ፣ ስለነዚህ ነገሮች ሲያማርር የሰሙት ሰው ካለም ሀኪም እንዲያናግር ይምከሩት፡፡