ስለ’ማካቶን’ ያውቁ ኖሯል?
Did You know about MAKATON?
አካል-ጉዳተኞች (People With Differently – abled) ወይም ልዩ-ፍላጎት ያላቸው ከፍተኛ የንግግር፣ የቋንቋ፣ የተግባቦት መዘግየትና እክል (Profound communication or language development Difficulties/Disorders) ላለባቸው በተለይ ከአዕምሮ ዕድገት እክሎች (Neurodevelopmental Disorders) ጋር የሚኖሩ ልጆች፤ እንደዚኹም በሚገባ ምዘና እና ምርመራ (Diagnosis and Assessment)፣ ቅድመ-መፍትሔ (Early Intervention) ፣ ተገቢ ቴራፒ ክትትልና ድጋፍ ካልተደረገና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች የንግግርና የተግባቦት ክህሎት መዘግየት ያይልባቸዋል። በዚኽም ምክንያት አንዳንድ ልጆች ለረጅም ጊዜና በዘላቂነት ስሜታቸውን መግለፅ ሲቸገሩ፣ ቃላት ማውጣት ሲሳናቸው፣ መግባባት ሲከብዳቸው ይልቁንም ‘NonVerbal’ ሲኾኑ እናስተውላለን።
ማካቶን (MAKATON) ከተግባቦት መሣሪያዎች አንዱ ሲኾን አስገራሚ እና ልዩ የቋንቋ ማዕቀፎችን የያዘ ነው። በውስጡም ምልክቶችን (Manual Signs)፣ ምስሎችን (Pictures)፣ ንግግሮችንና አጠቃላይ የተግባቦት ክሕሎቶችን፦ ትኩረት መሥጠት፣ ነቅቶ ማዳመጥ፣ ማስታወስ፣ መገንዘብ እና ሌሎች የቋንቋ፣ ሃሳብ ብሎም ስሜት የምንገልፅባቸው ነገሮችን እንዲጎለብቱ የሚያግዝ ነው። እንዲሁም በማካቶን ንግግርን እና ምልክት በጋራ በመጠቀም ድምፅ ማውጣት፣ በትክከል አለመናገር እና አጠቃላይ የቋንቋ መዘግየት ላለበት ማካቶንን በመጠቀም የተግባቦት ክሕሎቱን ማዳበር ይቻላል፡፡
ለምሳሌ፦ አንድ ልጅ መፀዳጃ ቤት መጠቀም ቢፈልግና ስሜትና ሃሳቡን በንግግር መግለፅ ቢቸገር በምልክት እጆቹን ተጠቅሞ (Manual Sign / Toilet) እንዲገልፅ ማድረግ።
ይኽ የመግባቢያ መሣሪያ ከእንግሊዛውያን የምልክት ቋንቋ የተቀዳ ቢኾንም ይዘቱና ዓላማው ግን የሚለይ ነው። በተለያየ ጊዜያት ተቃውሞ የገጠመው ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ እንደ አንድ የቴራፒ አማራጭ እየተሰጠ ይገኛል።
ዋኖስ መስፍን (@WanosMesfin)
የልዩ-ፍላጎት ትምህርት ባለሞያ
