እንባ እንባ ይለኛል
ይተናነቀኛል
ኦሮማይ ገጽ 371
ግን እንባ ከየት አባቱ
ደርቋል ከረጢቱ
ሳቅ ሳቅም ይለኛል
ስቆ ላይስቅ ጥርሴ
ስቃ እያለቀሰች
መከረኛ ነፍሴ
ድባቴ ከፍተኛ የሆነና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የሀዝን፣ የመከፋት፣ የመደበር ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ነው፡፡ ዐቢይ የድባቴ ህመም (major depressive disorder) ከድባቴ የህመሞች አይነቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በህይወታችን ላይ እክል ወይም ህክምና የሚሻ ጫና የሚፈጥር የሀዘን ወይም ፍላጎት የማጣት ህመም ነው፡፡ ይህ ሕመመ የድግግሞሽ (episodic) ባህሪ አለው:: ይህ ህመም የምንወደውን ሰው በሞት ብናጣ ከምናዝነው ሀዘን ከፍ ያለ እና የተወሳሰበ እክል (ችግር) የሚፈጥር ነው፡፡ በእርግጥ ሰው ሲሞትብን የምናዝነው ሀዘን ለረጅም ግዜ የሚቆይ እና የተጋነነ ከሆነ ወደ ድባቴ (depression) ሊያድግ ይችላል፡፡
የድባቴ ህመም ምልክቶቹ (depressive disorders)
አንዳንድ ህመምተኞች አልቅሰው ቢወጣላቸው ይመኛሉ፤ ግን እንባ አይወጣላቸውም፡፡ ህመምተኞቹ የድባቴን ምልክቶች ከ‹‹ኖርማሉ ሀዘን›› አስተካክልው ይለዩታል፡፡ በዚህ ሕመም የታመሙ ህጻናት ከትምህርት መቅረት፣ ከጓደኞቻው መነጠል ሲጀምሩ ወጣቶች ላይ ደግሞ በትምህርት አቀባበል ላይ መቀነስ፤ ራስን ስለማጥፋት ማሰብ፣ ወደ ሱሶች መግባት፣ ጸረ ማሕበረሰባዊ ባሕረያትን መላበስ እና ከቤት ወጥቶ ማደር ይጀምራሉ፡፡ ጎልማሶች ምልክቶቹን በስፋት የሚያሳዩ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ግን ሁኔታቸውን ሰለሚደብቁ ህመማቸው ሳይታወቅላቸው (እንደውም ተጫዋች፣ ሳቂታ፣ ስኬታማ ሁነው ወይም መስለው እየኖሩ) ራሳቸውን አጥፍተው ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ‹‹እከሌን ምን አጋጥሞት ነው›› ‹‹ምን የመሰለች ተጫዋች ልጅ እንዴት እንዲህ ታደርጋለች›› የሚሉ አስተያየቶች የምንሰማው ለዚህ ነው፡፡
ዋና ዋና ምልክቶች
አንድ ሰው፣ 2 ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ሳምንታት፣ ከሚከተሉት ምልክቶች ውስጥ 5ቱን ካሳየ በዚህ ህመም መያዙን ይጠቁማል፡፡
- ከፍተኛ የሆነ የመከፋት፣ የባዶነት፣ ተስፋ የመቁረጥ፤ የሀዘን ወይም ‹‹የድብርት›› ስሜት
- በፊት ያዝናኑ በነበሩ ነገሮች ላይ ለመዝናናት መቸገር ወይም ፍላጎት ማጣት
- የክብደት ወይም የምግብ ፍላጎት መቀነሰ weym mechemer
- የእንቅልፍ መታወክ
- የሰውነት መንቀራፈፍ
- ምንጩ ያልታወቀ ከፍተኛ ድካም weym hayl matat
- የ‹‹አልጠቅምም›› ስሜት ወይም የጥፋተኝነት ስሜት ወይም ራስን መጥላት
- ሃሳብን ለመሰብሰብ ወይም ለመወሰን መቸገር
- ራስን ስለማጥፋት በተደጋጋሚ ማሰብ፣ ማቀድ ወይም መሞከር
እንዚህ ምልክቶች ቢያንስ በ2 ሳምንት ውስጥ በአብዛኛው ቀን የሚከሰቱብን ከሆነ የአእምሮ ሃኪም ማማከር ያስፈልገናል፡፡
ተያያዥምልክቶች
- ስለራስ፣ ስለዓለም፣ ስለመጪው አሉታዊ አስተሳብ መያዝ
- የመጨነቅ ወይም የመታወክ ስሜት
- በሱስ ውስጥ ራስን ለመደበቅ መሞከር
- አካላዊ ምልክቶች ለምሳሌ፡- ራስ ምታት፣ የሆደ ድርቀት
- የሌለን ድምጽ መስማት ወይም የሌለን አካል ማየት
- ሰውን መጠራጠር ወይም ይጎዱኛል የሚል ምክንያታዊ ያልሆነ ፍራቻ