ህክምና እየተከታተለን ቢሆንም መሻሻል የማናሰaይበት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ፡፡ የሚከተሉጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
መደሀኒት በትክክል አለመውሰድ
በተለያዩ ምክንያቶች ታካሚዎች መደሀኒት በታዘዘላቸው መሰረት ላይወስዱ ይችላሉ
ምክንያቶች፡
- የመደህኒት ጎንዮሽ ጉዳት ፍራቻ
- መርሳት
- አንዳንድ የአእምሮ ህመሞች ራሳችን የአእምሮ ህመም እንዳለብን እንድንገነዘብ ሰለማይፈቅድሉን ጤነኞች ስለሆነን መደሐኒት አያስፈልገኝም ልንል እንችላለን
- የተሳሳቱ አመለካከቶች
ሱስ
- ለምሳሌ፤ ድባቴ/ድብርት ያለበት ሰው አልኮል ውስጥ ራሱን ሊደብቅ ይችላል፤ 80 በመቶ የሚሆኑት ስኪዞፍሬኒያ ያለባቸው ሰዎች ሲጋራ ያጨሳሉ፡፡
- ተጓዳኝ ሱስ ሲኖር ምልክቶቹ እንዲባባሱ እና መደሀኒቶች ባላቸው አቅም እንዳይሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡
ውጥረት
- ህመሙ እንዲነሳብን ምክንያት የሆኑ የህይወት ውጣ ዉረዶች (አስጨናቂ ነገሮች) ቀጣይነት ካላቸው ጥሩ መሻሻል ላናመጣ እንችላለን፡፡
ተጓዳኝ ሕመም መኖር
- ተጓዳኝ ወይም ተጨማሪ ሕመም በሚኖርበት ጊዜ አንዱ ሌላኛውን ሊያባብስ ወይም የሆነ ተጽኖ ሊፈጥር ይችላል
- ለተጓዳኝ ህመም የሚወሰድ ሌላ መድሀኒት ካለ መድሀኒቶቹ እርስ በእርሳቸው ሊቃረኑ ይችላሉ
በቂ ባልሆነ መጠን ወይምጊዜ መውሰድ
አንድ መደሀኒት ውጤታማ የሚሆንበት መጠን እና ለውጥ የሚያመጣበት ጊዜ አለው፡፡ በትክክለኛው መጠን እና ጊዜ የማይወሰድ ከሆነ ለውጡን ላናይ እንችላለን፡፡
- ለምሳሌ አብዛኛው የአእምሮ ሕመም መደሀኒቶች ለውጥ ለማሳየት ቢያንስ ለ2 ሳምንት አጥጋቢ ለውጥ ላያመጡ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም አእምሮ ውስጥ ያለውን መዛባት እስኪያስተካክሉ ያን ያህል ጊዜ ሊፈጅባቸው ይችላል፡፡
- ስለዚህ አንድ መድሀኒት አልሰራም ከማለታችን በፊት ቢያንስ ከ 1ወር እስከ 2 ወር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡
ምግብና መጠጦች
አንዳንድ ምግብና መጠጦች ካንዳንድ መድሀኒቶች ጋር ላይስማሙ ይችላሉ፡፡ መደሀኒቱ እንዳይሰራ ሊያደርጉት ወይም በሽንት ወይም ሰገራ …. መልክ እንዲወገድ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
የምርመራ ስህተት
ተመሳሳይ ምልክት የሚያሳዩ ህመሞች ስለሚኖሩ በተለያዩ ምክንያቶች (በተለይ ከምርመራ ጊዜ እጥረት ጋር ተያይዞ፣ ታማሚዎች ምን ለሀኪሙ ማስረዳት እንዳለባቸው አለማወቅ፤ የልምድ ማነስ፣ መመርመሪያ መሳሪዎች አለመኖር….) ምርመራው ላይ ስህተት ሊሰራ ይችላል፡፡ ስለዚህ ተገቢውን መድሀኒት ላይታዘዝ ይችላል፡፡
ዘግይቶ ወደህክምና መሄድ
ቶሎ ወደህክምና አለመሄድ ህመሙ ስር የሰደደ እንዲሆን ሰለሚያደርገው ለህክምና አስቸጋሪ እየሆነ ይመጣል፡፡