የሆነ ቀን ማታ ከክላስ እየተመለስኩ ሰፈር ልደርስ አካባቢ የቀለጠ ድንገተኛ ጩኸት ሰማሁ እና ጩኸቱ ወደተሰማበት ጊቢ ሮጬ ሔድኩ። አንድ በአስራዎቹ እድሜ የሚገኝ ልጅ ራሱን አጥፍቶ ተገኘ። ያሳዝናል አይደል? ከዚህ በላይ የምር ያሳዘነኝ የሰዉ response ነው!
በቤተሰቡ የድንጋጤ ጩኸት የተሰበሰቡ የመንደሩ ሰዎች አጠገቤ እንደቆሙ “ምን ሆንኩ ብሎ ነው አሁን?”፣ “የበርበሬ ወጪ የለበት የጨው፥ ቅብጠት ካልሆነ በቀር”፣ “ጨካኝ ነው ለቤተሰቦቹ እንዴት አያስብም?”… ሲሉ መስማት ይበልጥ ይሳዝናል።
አዕምሮ ነክ ችግሮች ትልቁ ጉዳታቸው እንደሌሎቹ በሽታዎች አለመሆናቸው፣ ማለቴ አካላዊ አለመሆናቸው ይመስለኛል። ብዙዎቹ ምልክቶች ከባህሪ ጋር ስለሚምታቱ፣ “እሱ/እሷ ልማዱ/ዷ ነው” እየተባለ ከመታለፍ ባለፈ የሚረዳ እና የሚረ’ዳ ሰው ማግኘት ይከብዳል። ወለም ያለህ እንደሆነ ግን “ልሽህ፣ ልደግፍህ” ባዩ ብዙ ነው።
ከልብ ስብራት ይልቅ የእግር ወለምታ more sense ይሰጠናል፤ ምክንያቱም ወለምታ physical evidence ሊቀርብለት ይችላል… ማለቴ አላምን ባይ እንኳን ካለ x-ray ተነስተህ ታሳየዋለህ። ግን የልብ ስብራትና የአዕምሮ መታወክ ታማሚው ሸፋፍኖ ሊደብቀው ከመቻሉም በላይ ቢናገሩት ራሱ አጉል የስም ተቀጥያ ያሰጣል በሚል ፍራቻ ዝምታን ያስመርጣል። “Am I being dramatic? Am I just seeking attention?” በሚሉ ጥያቄዎች ምክንያት አዕምሮን ዝም ለማሰኘት መጣር እና “normal” ለመሆን መሞከር የተለመደ ነው።
የድህነታችን ሰፊ እጅ እዚህም ጋር ሳይዳብሰን የቀረ አይመስለኝም። እንኳን በፊደል መቁጠሩ ያልገፉት ወላጆቻችን ቀርቶ ተምረናል የሚሉ እኩዮቻችን ብናስረዳቸው ብዙ የማይገቧቸው ነገሮች አሉ። ምክንያቱም እንኳን የአዕምሮ ደህንነት፣ በቀን ሦስቴ መብላት ራሱ እንደቅንጦት (luxury) የሚቆጠርባት ሀገር ውስጥ ነዋ የምንኖረው! ሌላውን ትተን “depression አይደለም ብሮ … ርቦህ ነው ብላበት ይተውሀል” የሚሉ ፖስቶችን ስንት ጊዜ አየን?
በቀላሉ መፈወስ የሚችሉ ህመሞች ለከፋ የአእምሮ ህመም ወይም ለሞት ሲዳርጉ ከንፈር መምጠጥ ምንም አንደማይፈይድ ማህበረባችን ገና የገባው አይመስልም። እና አዎ Mental health is not a luxurious thing, it’s a necessity!!
ፈረንጅ እግዜር ይስጠው እኛ የማናውቃቸውን ብዙ በሽታዎች በቅጥ ከማወቅና ከመሰነድ አልፎ መድሃኒቶቹንም ቀምሞ አዘጋጅቶልናል። ግን እኛ መታከም ለምን እንደምንፈራ አይገባኝም!
ጠበሉም ፀሎቱም ጋር መሄዱ ጥሩነቱ እንዳለ ሆኖ ሀኪም ጋር መሄድ ከኃጢአት እኩል የመቆጠሩ ነገር ያስገርማል። በጥቂት ፕሮፌሽናል እገዛ የሚስተካከሉ ችግሮች በዳተኝነት ምክንያት ሲብሱ ሲባባሱ ማየት ያሳዝናል። Anxiety disorders, personality disorders, depression and bipolar disorders, ADHD (attention deficit hyperactivity disorder)… የሚባሉትን አዕምሮ ነክ ሕመሞች ስማቸውን እንኳን በቅጥ የምናውቅ ስንቶቻችን ነን?
ብቻ We should normalize seeing professionals, getting treatment and taking medications!
እና ከሁሉም በላይ ስለራሳችን ስንል ራሳችንን ማበርታት ያለብን ይመስለኛል። You should be your own priority! I should be my own priority! በኛ መጎዳት ውስጥ የሚጎዱ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም፣ መጀመሪያ የጉዳቱ ሰለባዎች እኛው ነን! “የእኔን ደህንነት የሚነካ የማንም expectation ቢሆን ገደል መግባት ይችላል!” ማለት መልመድ ያለብን ይመስለኛል። በቃ ለራሳችን መቆም አለብን!
ተስፋ እንዳለ ለራሳችን ማሳየት አለብን፣ አንዲትም እርምጃ ቢሆን ወደፊት ፈቀቅ ለማለት መታገል አለብን። የእኛን ያህል ማንም እኛን ሊረዳን አይችልም! I should stand for myself! You should stand for yourself!!
ግን ደግሞ ቢመርረንም ልንውጠው የሚገባን ሀቅ ያለ ይመስለኛል። ሁሉም ሰው ለየራሱ ሕይወት ተጠያቂ ነው! ምንም ብንፍጨረጨር ልንቀይረው የማንችለው ሀቅ ፣ ልናድናቸው የማንችላቸው ሰዎች አሉ አንዳንዴ። ስለዚህ ስላለፍነው እና ስላለፉት ራሳችንን እየወቀስን መኖር የለብንም። Everyone is responsible for his own actions!
የሚበጀን ስለወደፊቱ መጨነቅ ነው። በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ግድ ይሰጠናል ወይ? ጓደኞቻችንን እንሰማቸዋለን ወይ? ሲደብራቸው “አለሁ፣ አይዞኝ” እንላቸዋለን ወይ? ሊደረግልን የምንፈልገውን ለሰዎች እናደርጋለን ወይ?
እኛ እግዜር አይደለንም፣ ለሁሉም ሰው መፍትሔ የለንም። ሁሉንም ሰው አድምጠን አንችለውም፤ ግን ቢያንስ ሁላችንም በዙሪያችን ላሉ ጥቂት ሰዎች concerned እንሁን።
Idk why I’m ranting all this nonsense. ምናልባት የሆነ ሰው ከጠቀመ ብዬ ነው!
እና If you’re struggling, you should know this…You ain’t alone! ብቻችሁን አይደላችሁም! ብዙ ታጋይ አለ! ምንም እንኳን “ሁሌም ከጎናችሁ እሆናለሁ” ምናምን ብዬ ቃል የምገባበት አቅም ባይኖረኝም። ግን I will try at least! Genuinely እርዳታ የምትፈልጉ ከሆነ ብዙ ሊረዷችሁ የሚፈልጉ ሰዎች እዚህ አሉ – Reach them out! ከሁሉ በላይ ራሳችሁን እርዱ! Stand for yourself!
እርሶ ወይም ወዳጅ ዘመድዎ በራስ ማጥፋት ሀሳቦች እየተጨነቁ ከሆነ እባክዎን በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ ወይም የስነ-ልቦና ማዕከል በመሄድ የባለሙያ ድጋፍ እና ሪፈራል ያግኙ።
ለአእምሮ ህክምና ተጨማሪ መረጃ: https://bit.ly/3KTRnDr
በYonathan Getachew (Software Engineer)
www.facebook.com/YoniiBoss