ባይፖላር ህመም አይት 1 ከሽቅለት ሞዕራፍ ወደ ዐቢይ ድባቴ ምዕራፍ እንዲሁም ከድባቴ ምዕራፍ ወደ ሽቅለት ምዕረፍ የሚገለባበጥበት ህመም ነው፡፡ በአጭሩ፤ የሆነ ወቅት በጣም ደስተኛ መሆን በሌላ ጊዜ ደግሞ በጣም ሀዘንተኛ መሆን ማለት ነው፡፡
የስሜት-ምዕራፍ (Mood episodes) ስንል የተለየ ሃይል፣ ስሜት፣ አስተሳሰብ፣ ሃይልና ባህሪ የሚንጽባረቅበት ወቅት ማለታችን ነው፡፡ ለምሳሌ የሽቅለት ምዕራፍ (Manic episodes) በሆነ የተወሰነ ወቅት የሚታይ እና የተጋነነ የደስተኝነት፣ የተስፈኝነት፣ የንጭንጭ፣ በራስ የመተማመን ይንጸባረቁበታል፡፡ በሽቅለት ምዕራፍ (ወቅት) የሚኖረን አስተሳሰብ፣ ድርጊትና ስሜት በድባቴ ወቅት ከሚኖረን ስሜት፣ አስተሳሰብና ድርጊት ሊለይ ወይም ሊቃረን ይችላል፡፡
ባይፖላር ህመም አይት 1 ያለበት ሰው ለተወሰኑ ሳምንታት ወይም ቀናት በደስታ ይጥለቅለቃል፣ በፍጥነት ይናገራል፤ የዕንቅልፍ ፍላጎቱን ያጣል፣ ራሱን ይኮፍሳል… ለተወሰነ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ይቆይና ወደ ቀደሞ (normal) ማንነቱ ለትንሽ ጊዜ ይመለሳል ከዚያን ከፍተኛ የሆነ ድብርት ውስጥ ይገባል፡፡ (የቀደሞ ማንነቱ ስንል ህመሙ ከመጀመሩ በፊት የነበረው ባህሪ ማለታችን ነው) እንዚህ ስሜቶቹ ይቀሩና (ሙሉ ለሙሉ ላይቀሩም ይችላሉ) በተራው ደግሞ ማዘን፣ መሰላቸት፣ እንቅልፍ እምቢ ማለት፣ ራስን መጣል፣ አልጠቅምም ማለት፣ ራስን ለመጉዳት መሞከር፣ የምግብ ፍላጎት እና ክብደት መቀነስ….ይጀምራል፡፡ ይህንን ጊዜ የድባቴ ምዕራፍ (depressive episode) እንለዋለን፡፡ ይህ የድባቴ ወቅት ለተወሰኑ ወራት ይቆይና ወደ ቀደሞ ባህሪያችን ለትንሽ ጊዜ ይመለሳል ወይም ወይም ወደ ሽቅለት ምዕራፍ ወዲያዉኑ ይሸጋገራል፡፡
ሕመምነቱ ምኑ ላይ ነው?
- ምን እንዳገኝ ሳታውቅ ስሜትህ እየተለዋወጠ ብትኖር ምን ይሰማሃል? እንዚህም ታማሚዎች ‹‹ምን እየሆንኩ ነው፤ ስሜቴ በቀላሉ የሚለዋጠው ለምንድን ነው›› ወደሚል ጭንቀት ይከታቸዋል፡፡ ይህ ጭንቀት ደግሞ ወደ መረበሽ፣ ራስን ማግለል፣ ሱስ መጀመር፣ ራስን ወደ መጥላት ያመራል፡፡ ራስን ማጥፋትም ሊከተለው ይችላል፡፡ በዓለም ላይ ራሳቸውን ከሚያጠፉት ሰዎች ውስጥ 25% ምክንያታቸው ይህ ህመም ነው፡፡
- በኑሮ፣ በስራ፣ በማህበራዊ ግንኙትት፣ በቤተሰብ ወይም ሌሎች ጠቃሚ የሕይወት ገጽታዎች ላይ ችግር ስለሚፈጥር
- ተደጋጋሚ የሆኑ ራስን የማጥፋት ሀሳቦች እና ሙከራዎች ሰለሚኖሩ
- የእንቅልፍ ችግር ስለሚያስከትል
- ሕይወትን አደጋ ላይ ስለሚጥል
- የጭንቀት ምልክቶች ጋር:
- ሕመምተኛው ጭንቅ ጭንቅ የሚል ስሜት፣ የመረበሽ፣ የመቁነጥነት፣ ‹‹ራሴን መቆጣጠር ሊያቅተኝ ነው›› የሚል ስሜት ሊሰማው ወይም ትኩረቱን መሰብሰብ ያቅተዋል
- ለመቋቋም የሚያስቸግር የስሜት ለውጥ ሰለሚያመጣ
- የሰውነታችን አሰራር ለውጥ ስለሚያመጣ (physiologic change)
- ሌላ ደባል ሕመሞችን ሰለሚያመጣ
ስርጭቱ
በዓለም አቀፍ ደረጃ፡ በአንድ ክፍል ውስጥ 200 ሰው ቢቀመጥ ከነዚያ ውስጥ እስከ 5 የሚደርሱት ይህ ህመም ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ በወንዶችም በሴቶችም እኩል የመከሰት እድል አለው ነገር ግን ወንዶች ላይ የሽቅለት ምዕራፍ ሲበዛ ሴቶች ላይ ደግሞ የድባቴ ምዕራፎች ይበዛሉ፡፡ ከ5-50ዓመት ባለው የእድሜ ክልል መከሰት ቢችልም በአማካይ 30 ዓመት ላይ ይከሰታል፡፡ ብቻቸውን በሚኖሩ እና በተፋቱ ሰዎች እንዲሁም ከፍ ያለ ኢኮኖሚ ባላቸው ሰዎች ላይ ይበዛል፡፡
ምልክቶቹ
በሽቅለት ወቅት
• መነጫነጭ
• ልቅ የሆኑ እንቅስቃሴዎች (ሩካቤ፣ ማህበራዊ ግንኙነት፣ አባካኝነት…)
• የእንቅልፍ ፍላጎት ማነስ
• ወሬኝነት
• ቅብጥብጥneት
• ራስን መኮፈስ
• በፍጥነት ማውራት
በድባቴ ወቅት
• ከላይ ያለውን የድባቴ ምልክቶች ያንብቡ…. ይህንን ይንኩ
ሕክምናው
ዉጤታማ ህክምና አለው፡፡ የህክምናው ዓላማ፡- ምልክቶቹን መቆጣጠር፣ ተመልሰው እንዳይመጡ መከላከል፣ የተረጋጋ ስሜት እንዲኖር፣ የስራ እና የማህበራዊ ግንኙነት አቅም መገንባት… ነው፡፡
የመደሀኒት ህክምና
የንግግር ህክምና እንዲሁም መንፈስ አረጋጊዎች (mood stablizares) የሚባሉ መደሀኒቶች አሉት፡፡
የመድሀኒት ህክምናው ሁለት ክፍል ሲኖረው፣ በመጀሪያው ክፍል አስጊ የሆኑተን የህመመሞች ምልክት መቆጣጠር (acute management phase) ሲሆን ሁለተኛው ክፍል ምልክቶቹ ተመልሰው እንዳይከሰቱ መከላል ነው (prophylaxis). እንደ ህመምተኛው ሁኔታና የህመሙ ምልክቶች ተገቢውን መደሀኒት ሀኪሙ ያዛል፡፡
የንግግር ህክምናዎች
Interpersonal and social rhythm therapy (IPSRT)
* የህመምተኛውን የዕለት-ዕለት እንቅስቃሴዎን መደበኛ ማድረግ ላይ ያተኩራል፡፡ ለምሳሌ መመበጊያ ሰዓት፣ የእንቅልፍና የመንቂያ ሰዓት፤ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ…፡፡ መደበኛ የዕለት-ዕለት ክንዉኖች ስሜትን ለመቆጣጠር ይረዳሉ፡፡
*የግንዛቤና ባሕሪ ህክምና (Cognitive behavioral therapy (CBT))
* ይህ የንግግር ክህምና አይነት ጤናማ ያልሆኑ፣ አሉታዊ አስተሳቦችንና ድርጊቶችን መለየት ላይ ያተኩራል፡፡ ለህመሙ መነሾ የሆኑ ስነ ልቦናዊ ጫናዎችን ይመረምራል፡፡ በመጨረሻም ትክክል ያልሆኑ አስተሳሰቦችን ያስተካክላል፡፡ እንዲሁም፤ በአስጨኛቂና አናዳጅ ወቅቶች እንዴት ጭንቀትን መቆጣጠር እንዳለብን ያለማምዳል፡፡
ልቦናዊ ትምህርት (Psychoeducation)
* ይህ ስለህመሙ ልብ እንድናደርግ ያግዘናል፤ የህመሙን ባህሪ፣ መነሻ እና ሁኔታ እንዲሁም የህክምናውን አወሳሰድ ለህመምተኛው፣ ለቤተሰብ፣ ቅርብ ጓደኛ…. በማስረዳት ሕመምተኛው ተገቢውን እገዛ እንዲያገኝ ይረዳል፡፡
ቤተሰብን ያተኮረ ህክምና (Family therapy)
* ይህ ቤተሰብን በማሳተፍ፣ በቤተሰብ ውስጥ ያሉ ጫናዎችች፣ ጥሩ ያልሆኑ ግንኙነቶን፣ አረዳዶችን በማስተካከል…የታማሚዎውን ህክምና ለማሻሻል ይሰራል፡፡