ድብርት በድባቴ ህመም እና በባይፖላር ህመም ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ በባይፖላር ውስጥ ያለ ድብርት ከደስታው (ሽቅለት) ቀድሞ ከመጣ ምርመራው የመሳሳት እድል አለው፡፡ ስለዚህ የባይፖላር ወይስ ዪኒፖላር መሆኑን እንዴት መለየት እንችላለን?
ዩኒፖላር ወይስ ባይፖላር ድብርት?
ድባቴው ዩኒፖላር ወይም ባይፖላር መሆኑን ለመለየት የሚጠቁሙ ነገሮች አሉ፡፡ የሚከተሉት
የሁለት ዋልታ ድባቴ (bipolar depression) መሆኑን የሚጠቁሙ ነጥቦች ናቸው፡፡
- የባይፖላር ዲፕረሽን በአማካኝ ከ3-6 ወር ሲቆይ ዩኒፓላር ዲፐረሽን ከዓማካኝ 12 ወራት ይቆያል፡፡ ስዚህ ቶሎ የሚቀያየር ወይም ሄድ መጣ የሚል ከሆነ ባይፓለር ዲፕረሽን ሊሆን ይችላል
- ያጋጠመዎት ከወለዱ በኋላ ከሆነ ባይፖላር ዲፕረሽን ሊሆን ይችላል
- ከእውነት አፋች ምልክቶች (psychotic symptoms) ቶሎ ከጀመሩት
- በእድሜ ቶሎ ከጀመረ
- በድባቴ መደሀኒቶች ለውጥ የማያሳይ ከሆነ
- በድባቴ መድሀኒት ወደ ሽቅለት የሚገለበጥ ከሆነ
- ቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ የህመም ታሪክ ካለ