1-
ሰው ሲሞት እንደአንድ ጤነኛ ሰው አዝናለሁ። ግን ለምን እንደኹ እንጃ በተለይ ወጣት ሰው ራሱን አጥፍቶ ሲሞት ይበልጥ ያሳዝነኛል። That really bothers me! ለምን? ምን ቢያጋጥመው ነው እስከሞት ያስጨከነው? ተራ curiosity ይሁን የመርዳት ፍላጎት ለይቼ ባላውቅም!
፨
ደግነቱ በትንሹም ቢሆን አውቀዋለሁ፤ ያው ጦርነት እያመሳት ባለች ድሃ ሀገር እንደሚኖር ፣ በግሉም ብዙ ትግሎች እንዳሉበት አንድ ወጣት እኩያዬ ምን ሊሰማው እንደሚችል በትንሹም ቢሆን አውቀዋለሁ።
፨
የሆነ አንድ የተለመደው ዓይነት ቀን ጠዋት ወደክላስ እየሄድኩ እያለ ነው ድንገት መድከሜ የገባኝ – There was something different about me.
ማለቴ ከዚያም በፊት I’ve been struggling for years ምናምን እኮ…I know all those ኮንፊደንስ የማጣት፣ inferiority፣ Overthinking፣ anxiety፣ feeling down and depression ሺትስ… ግን በቃ ያ ቀን ነው የሆነ ነገሬ seriously እንደተሰበረ የገባኝ… አለ አይደል this Yonathan is totally a different one ምናምን ያልኩት።
መተንፈስ ደክሟችሁ ያውቃል? That literally happened to me… ማለት ትንፋሽ አጠረኝ ምናምን ሳይሆን literally መተንፈስ ስራ ሆነብኝ…
“እንዲያው ምን ቢያታክት ሀሞቱን ቢያፈሰው
መተንፈስ ይደክመዋል ወይ ሰው?”
… የምትል ግጥም ሁላ ፃፍኩ 😅 ማለቴ ብዙ የድካም አይነት አውቃለሁ ያኔ ይሰማኝ የነበረው ድካም ግን የተለየ ነው።
That day I realized በሕይወት ያወጣችኋት እያንዳንዷ አቅም በኋላ እንደምትቀናነስ … አለ አይደል ቀላል ናት ብላችሁ ያሳለፋችኋት እያንዳንዷ ጠጠር የምታህል ችግር ኋላ ከቢጤዎቿ ጋር ተሰብስባ ቋጥኝ ሆና መምጣቷ አይቀርም።
ግን ከሁሉ በላይ የሚጎዳው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? PRETENDING!! Since I was that “perfect” kid ሰዎች ለኔ የሣሉትን አይነት ሥዕል ለመሆን መፍጨርጨር ነበረብኝ …fake it till you make it እንዲሉ። በዛ ላይ ችግሬን ከማውራት ይልቅ ውስጤ መያዝ የምመርጥ ሰው ነኝ። እና በሳቅና ሂውመር የተሸፈኑ ብዙ ሕመሞች የሆነ ቀን ሰብሰብ ብለው ይመጡና ድጌ ቀና እንዳትል አድርገው ያደቁሀል።
I knew I can’t be the old me… I felt like I lost my passions, dreams and all. Oh man! That time was though! I was literally drained off… idk if I’m explaining it well or exaggerating it. ከብዙ ነገር ሸሸሁ… Even from my fellowship! And I was a leader there… ግን በቃ ስልኬን አጥፍቼ ጠፋሁ… ክላስም ድሮም ድሮ ነኝ እንኳን እንዲህ ሆኜ 😂 እና በቃ የሚታየኝ ቤቴ ነበር…that’s the only place i feel safe (still 😁) ድብብቆሽ በሉት…
በተለይ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ It was hell… ጊቢ ተጀመረ፣ GC የመሆን ጭንቀት ተጨመረበት፣ ከዚያ final project የምንሰራበት group አጣሁ፣ ያበደ ጨጓራዬ ተነሳብኝ ምናምን፣ plus some family cases…በቃ በትክክል function እያደረኩ እንዳልሆነ ገባኝ… ስልኬን ዘጋሁ። እና የሆነ ቀን በር ብቻዬን ቤት ተኝቼ እያለ በር ተንኳኳ እና ስከፍት it was my friend from ጊቢ (ከ5 ኪሎ ቃሊቲ ድረስ መጣ 😅) እና ብዙ አወራን ምናምን… ግን እውነት ከወሬው በላይ knowing that የሆነ ሰው ለኔ ተጨንቆ ቤቴ ድረስ ሊፈልገኝ እንደመጣ ማሰቡ ብቻ በጣም ብርታት ሰጠኝ! እንዲህ አይነት ሰዎች ይብዙልን!!
የሆነ ጊዜ I tried counselling ምናምን። ማለቴ ለእኔ አይነት prideful ሰው “I need help” ብሎ መሄድ ትልቅ courage ይጠይቃል… sadly በቃ አለ አይደል ከአንድ ቀን አነቃቂ ምክር የበለጠ ብዙም አላገኘሁም… What I needed was a good mentor to whom I could be accountable for ምናምን ግን ያው ነገሮች እንደፈለጋችሁት አይሄዱም አይደል?
ብቻ ምን ልላችሁ ነው – ሁላችንም በብዙ ነገር ውስጥ እናልፋለን። Painless life isn’t promised! ብቻ ለመበርታት እንታገል እንጂ!
፨
How I dealt with that time? What helped me?
ማንበብ – ያን ያህልም አንባቢ ባልሆንም ጥቂት enjoy ከማደርጋቸው ነገሮች አንዱ ማንበብ ነው። At least it helped me to escape from the pain of reality for moments.
People – oh my beloved friends! ተገናኝተን፣ roast ተደራርገን እና excessively ስቀን፣ ሲደብረን አውርተን፣ ወክ አድርገን መለያየት is therapeutic!
ሌላው ነገር perfectionist’ነቴን ከላዬ ገፍፌ ለመጣል ሞከርኩ። ማለቴ ማስመሰል የለብኝም ብዬ ወሰንኩ። የሌለ ግብዝ ነበርኩ! እና Intentionally ራሴን በጽሑፎቼ ምናምን vulnerable ማድረግ ጀመርኩ። ማለቃቀስ ጀመርኩ! ጽሑፎችን suicidal ናቸው እስክባል ድረስ ውስጤ ያለውን የቆየ ሀሳብ ማውጣት ጀመርኩ። And that really helped me. እና ግጥም መጻፍ isn’t luxury for me! It’s kinda a painkiller!
And ማልቀስ? You have no idea how that helps! አለ አይደል ሁዲ ለብሶ፣ በጨለማ ሙዚቃ እየሰሙ እያለቀሱ ወክ ማድረግ… ain’t that dramatic? 😂😂 Yeah try it – it’s beautiful!
፨
Yet still it’s freaking hard!! መኖር የሚያስጠላበት ጊዜ አለ፣ out of no where ቅልብሽ የሚልበት ጊዜ አለ፣ ማሰብ የሚያቅትበት ጊዜ አለ፣ ሰው ማየት የሚያስጠላበት ጊዜ አለ፣ ከአልጋ መውረድ የሚከብድበት ጊዜ አለ፣ እልም ያለ ገጠር ሄዶ ከሰው ርቆ መክረም የሚያሰኝበት ጊዜ አለ፣ ሞት የሚናፍቅበት ጊዜ አለ፣ ተስፋ የሚጠፋበት ጊዜ አለ
Yet all this ሺት is not above us and this shall pass too!!
እና አሁንም ቢሆን በእኔ በኩል የመሞት እቅድ የለኝም 😅 ለነገሩ የምንም ነገር እቅድ የለኝም! ምንም ባይኖር ወደፊት ስለማነባቸው መጽሐፍት፣ ስለማያቸው ቆንጆ ቲያትሮች፣ ስለማሳልፋቸው heavenly moments እና ስለማገኛቸው ፀዴ ሰዎች ስል እኖራለሁ።
እና እናንተም የመሞት እቅድ አይኑራችሁ! እየታገሉ መኖር ይሻላል አይደል? ከሞት ምንም አይገኝም አይደል?
እና ያው ኤልያስ እንዳለው ነው… “ኑር ባታምንም
ላንተ ባይመስልም
ለከንቱ አልተፈጠርክም”
Cheers for the coming years we struggle together 🍻
© ዪናታን ጌታቸው