ንዑስ-ሽቅለት (hypomania) ልክ እንደ ሽቅለት (mania) የበዛ፣ ድስተኝነት፣ መቅበጥበጥ፣ መነጫነጭ…. ነው፡፡ ነገር ግን ከሽቅለት ቀለል ያለ እና ቢያንስ ከአራት ቀናት በላይ የሚቆይ ነው፡፡ (ሽቅለት ቢያንስ ለ1 ሳምንት መቆየት እንዳለበት ልብ ይሏል!)
ህመምተኛው ግልጽ የሆነ፣ ቤተሰቡ ወይም ሌላ ግለሰቡን የሚያውቀው ሰው የሚለየው የበዛ የባህሪ ለውጥ ያሳያል፡፡ በማህበራዊ ግንኙነት ላይ፣ ትዳር ላይ፣ ስራ ላይ ወይም ሌሎች ጠቃሚ ነገሮች ላይ መስተጓጎል የሚያመጣ ቢሆንም ሽቅለት ከሚያመጣው እክል/ችግር ግን ያነሰ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሰዎች ከሕመም ምልክትነት ይልቅ እንደበጎ አጋጣሚ ስለሚቆጥሩት ለሀኪም ላይናገሩት ይችላሉ፡፡ ከፍ ያለ የስራ ቅልጥፍናና ችሎታ እንዲሁም የፈጠራ አቅም ሊኖርም ይችላል፡፡
ምርቃና ከሽቅለት በሚከተሉጥ ነጥቦች ይለያል
- ቢያንስ ለ4 ቀናት መታየት አለበት
- ስራ ወይም ማህበራዊ ግንኙነት ላይ አነስ ያለ እክል መፍጠሩ
- ከእውነታ የወጡ እምነቶች ወይም መረዳቶች የሌሉት መሆኑ
ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ)