(አንዳንድ ቃላቶች በዚህ ጹህፍ አዘጋጅ ወደ አማረኛ የተመለሱ ናቸው፡፡ የተሻለ ትርጉም ካለው እርሱን እንጠቀመው)
ሲሲሊያ ሚክጎው ትባላለች፡፡ ፐልሳር የሚባል ግኝት ያገኘች የስነ ፈለክ ተመራማሪ ናት፡፡ ከስኪዞፍሬኒያ ጋር ያደረገችውን ግብግግብ እንዲህ ትናገረዋለች
ስኪዞፍሬኒያ የብዙ እክሎች ስብስብ የሆነ የተዛባ እውነታ የሚፈጥር ህመም ነው
- በአስተሳሰብ፣ አረዳድ፣ እንቅስቃሴ እና የእርስ በእርስ ግንኙነቶች ላይ ለውጥ የሚያመጣ
- በለጋነት እድሜ የሚጀምር እና ስር እየሰደደ የሚሄድ
- ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ፤
- በህመምተኛው እና ቤተሰቡ ላይ ትልቅ መቃወስ የሚፈጥር
- ኢኮኖሚያዊ ቀውስ
- ስራ አጥነት እና ቤት አልባነትን (ጎዳና ኗሪነት)
- የህክምና ወጪ
- እየሰፋ የሚሄድ ስቃይ ያለው
- እየቀነሰ የሚሄድ ማሕበራዊ ግንኙነት
- ራስን ማግለል፣ የዕለት-ዕለት ስራዎቸን ለማከናወን መቸገር
- ከፍተኛ የሱስ ደባልነት እና ራስን የማጥፋት ፍላጎት (ይህ ህክምናው ላይ ያለውን ውጤት ይቀንሰዋል)
ስርጭቱ
- ከ100 ሰው 1 ሰው ላይ የሚከሰት (ከታመሙት 0.05በመቶዎቹ ብቻ ነወ ህክምና ያገኙት)
- ወንዶችም ሴቶችም ላይ እኩል ስርጭት ያለው፡፡ ነገር ግን በአብዛኛው ለወንዶች ከ10-25፤ ለሴቶች 25-35 ባለው የእድሜ ክልል ውሰጥ የሚከሰት
- በሴቶች የተሻለ ውጤት ይኖረዋል፡፡
- 80በመቶ የሚሆኑት ሌሎች ተጓዳኝ ሕመሞች አሉባቸው
- አስጊ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ (ከፍተኛ የሆነ ራስን የማጥፋት ሁኔታ)
መንስኤ/አጋላጭ ነገሮች
- ስነ-ሕይወታዊ (biological)
- ️ በአንጎል ውስጥ ያሉ ኬሚካሎች ከመጠን በላይ መብዛት ወይም ማነስ
- ️ የአንጎል ክፍሎች እና የነርቭ ህዋሶች መጎዳት እንዲሁም መመንመን
- ️ ዘረመል (በዘር ሀረግ)
- አከባቢያዊ ተጽኖዎች ካልተጨመሩበት በስተቀር ዘረመል ብቻውን ለህመሙ ላያጋልጥ ይችላል፡፡
- ️ በእርግዝና እና ምጥ ወቅት የሚኖሩ ችግሮች
- ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ (Social and psychological)
- ️ ስደት
- ️ ከተሜነት እና የህዝብ ብዛት
- ️ በክረምት ወቅት መወለድ
- ️ እድሜያቸው ከ50 በላይ ከገፋ አባት መወለድ
- ️ አስቸጋሪ የህይወት ውጣ ውረዶች
- ️ የእናት እንክብካቤ ዕጦት
- ️ ለተቃራኒ ጾታ ልጆች አድሎ ወይም የተለየ እንክብካቤ ማድረግ
- ️ በእናትና አባት መካከል የሚኖር የተካረሩ አለመግባባቶች
- ️ ግልፍተኛ ወይም ነቃፊ ወላጆች
ምልክቶቹ

ፕሮፌሰር ጆን ናሽ
በስኪዞፍሬኒያ ሲታከም የነበረ የሂሳብ ሊቅ
- ብዙ ምልክቶችን አሰባስቦ የያዘ ነው (አንድ ታማሚ ከስር የተጠቀሱትን ምልክቶችን በሙሉ ያሳያል ማለት ግን አይደለም)
- አዎንታ ምልክቶች (positive symptoms)
- ሀሉሲኔሽን (hallucination)
- ስለ ሀሉሲኔሽን ያንብቡ፡ t.me/Gashaw_Aweke/72
- ዴሉዥን (delusion)
- ስለ ዴሉዥን ያንብቡ፡ t.me/wemindETH/60
- የንግግር እክል (disorganized speech)
- የተዘበራረቀ ንግግር (derailment)፡ ቅደም ተከተላዊ ግንኙነት የሌላቸውን ሀሳቦች በአድ ላይ መናገር፡፡
- ጠርዝነት (Tangentiality)፡ የሚገናኙ ሀሳቦችን መናገር ቢችል እንኳን የተፈለገውን ጉዳይ ጠርዝ ነካ አድርጎ መተው፡፡
- ዙሪያ ጥምጥም (Circumstantiality)፡ የማይሰፈልጉ መረጃዎችን ተናግረው ስለተፈለገው ጉዳይ ያወራሉ፡፡
- ማያያዝ (Clanging)፡ ቤት የሚመቱ ቃላትን መናገር፡ ለምሳሌ ጥቀረሻው. ኬሻው፣ እርሻው፤ ውሻው
- ፈጠራ (Neologism)፡ ትርጉም አልባ ቃላትን እየፈጠሩ መናገር
- ማስተጋባት (Echolalia)፡ ሌላ ሰው የሚናገረውን ቃላት እንደገደል ማሚቶ ማስተጋባት
- ሀሉሲኔሽን (hallucination)
- አሉታ ምልክቶች (negative symptoms)
- የደበዘዘ ወይም ልሙጥ የፊት ገጽታ (Blunted or Flat Affect)፡ ስሜት አልባ የሆነ የፊት ገጽታ
- ዝግ ያለ እንቅስቃሴ (Decreased spontaneous movements)
- የቀነሰ በአካል እንቅስቃሴ (የፊት ገጽ፣ እጅ፣ ጭንቅላት፤ እግር…) የመግባባት ችሎታ (Paucity of expressive gestures)
- የድምጽ ቃና እየለዋወጡ ስሜት ለመግለጽ መቸገር
- ራስን ማግለል (Asociality)
- የቀነሰ ወይም ግድየሌሽነት ያለው ማህበራዊ ግንኙነት (ቀስ በቀስ ራስን ወደመነጠል እና ጥቂት ቃላቶችነ ወደመናገር የሚያመራ)
- ያነሰ የሩካቤ ፍላጎት (Reduced sexual interests and activities)
- ወዳጅ የማፍራት ስሜት ማነስ
- የንግግር እጥረት/ውስኑነት (Alogia)
- ብዙ ለመናገር አለመፈለግ (አጭር መልሶችን መስጠት…)
- በቂ መረጃ መስጠት አለመቻል (ብዙ ተናግሮም እንኳን)
- ጥያቄ ለመመለስ ብዙ መዘግየት
- ተነሳሽነት ማጣት (Avolition)
- ራስን ለመጠበቅ/ለመንከባከብ ፍላጎ ማጣት
- ስራ ላይ ትኩረት አድረጎ ለመቀጠል መቸገር
- ድካም ወይም አቅም ማጣት
- ድስታ ማግኛ መንገዶችን ማጣት (anhedonia): ድስታ ማጣት ወይም በፊት ደስታ በሚፈጥሩልን ነገሮች ለመደሰት መቸገር
- የደበዘዘ ወይም ልሙጥ የፊት ገጽታ (Blunted or Flat Affect)፡ ስሜት አልባ የሆነ የፊት ገጽታ
- ሌሎች ምልክቶች
- ድብርት፤ የጥፋተኝነት ስሜት፣ መቅበጥበጥ እና መሸበር
- ግልፍተኝነት (ስድብ፣ ሰው ለማጥቃት መፈለግ…)
- የማስታወስ ችግር
- ለመማር መቸገር