በ300 ዓዓ ገደማ senile dementia syndrome የሚል በግብጽ ጽሁፎች ላይ የተጻፈ የአእምሮ ሕመም ገለጻ እናገኛለን፡፡ ሂፖክራተስ mania and hysteria ቃላትን እንደ አእምሮ ሕመም አይነቶችንን አስተዋውቆ ነበር፡፡ ይሁንና እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የነበረው የአእምሮ ህክምና ሳይንስ እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡፡ የአእምሮ ህክምና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፍጥነት እያደጉ ካሉ የህክምና ዘርፎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በዋናነት ICD-11 (በዓለም ጤና ድርጅት የተዘጋጀ) እና DSM-5 (በአሜሪካ የሳይካትሪ ህብረት የተዘጋጀ) የሚባሉ የአእምሮ ሕመሞች መዘርዘሪያና መመደቢያ ሰነዶች አሉ
ከ300 የሚበልጡ የአእምሮ ሕመሞች በDSM5 ላይ ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ መመሪያው እነዚህን ህመሞች (የአእምሮ ጤና መቃወሶች) በ22 ዘርፍ ይመድባቸዋል፡፡